Photos

3-tag:People-1110px-slider

Home


ለጥበብ ቤተሰቦች፣

ቁራኛዬ፡ በህግ ከሄደች በቅሎዬ ያለህግ የሄደች ጭብጦዬ

ሲነርጂ ሃበሻ ፊልምና ኮሚኒኬሽን፣ መስከረም 19/2020

            የቁራኛዬ ፊልም መሪ ተዋናይት የምስራች ግርማ በቡርኪናፋሶ በተዘጋጀው በሶቲጉዪ አካዳሚ/Sotigui Academy ላይ የ2020
ምርጥ የምስራቅ አፍሪካ ተዋናይ ሆና ታጨች!

 የቁራኛዬ ፊልም ላይ ዓለሜን ሆና በመሪ ተዋናይነት ድንቅ ብቃቷን ያሳየችን የምስራች ግርማ በቡርኪናፋሶ በተዘጋጀው በሶቲጉዪ አካዳሚ/Sotigui Academy 2020 የምሽት ሽልማት ኢትዮጵያን ወክላ ስትታጭ ታላቅ ደስታ ይሰማናል፣ ይህ የፊልም ሽልማት በፊልሙ ዓለም የራሳቸውን ጉልህ አሻራ  ማስቀመጥ ለቻሉ ምርጥ አፍሪካውያንና አፍሪካዊ ዳያስፖራዎች  የሚሰጥ ሽልማት ነው፣ ይህ የፊልም ሽልማት ላለፉት 5 ዓመታት የፊልም ተዋናዮችን ዕውቅና በመስጠጥ ለተመልካቾቻቸው እንዲታወቁ በማድረግ ትልቅ ሚና ተጫውቷል፡፡ ዝነኛው Panafrican Festival of Cinema and Television of Ouagadougou (FESPACO) የዚህ አካዳሚ አጋር መሆኑ የሽልማት ስነስርዓቱን ከፍ ያለ ግምት ያሰጠዋል፡፡  

ቁራኛዬ ፊልም በሞገስ ታፈሰ ተፅፎ የተዘጋጀ ሲሆን ፊልሙ በኒው ዮርክ በተዘጃጀው የአፍሪካን ዳያስፖራ ኢንተርናሽናል ፊልም ፌስቲቫል (African Diaspora International Film Festival) ለዕይታ በቅቷል፤ በሲልቨር ስፕሪንግ በተዘጋጀው ኒው አፍሪካን ፊልም ፌስቲቫል (New African Film Festival) የፌስቲቫሉ መክፈቻ የነበረ ሲሆን፣ በግብፅም በተዘጋጀው ሉክሶር አፍሪካን ፊልም ፌስቲቫል (Luxor African Film Festival) ለዕይታ መብቃቱ ለሶቲጉዪ አካዳሚ/Sotigui Academy እንዲወዳድር እድል ፈጥሮለታል፡፡ ፊልሙ ሃገር አቀፍና አለም አቀፍ መክፈቻዎችን በአዲስ አበባ፣ በአሜሪካን፣ በእንግሊዝና በጀርመን ማድርጉ እንዲሁም በሀገር ውስጥ በርካታ እውቅናና ሽልማት ማግኘቱ የሚታወስ ነው፡፡ ፊልም በሃበሻ ቪው (www.habeshaview.com) አማካኝነት በሁሉም ሃገር በመታየት ላይ ነው፡፡  ፊልሙ በተሰራበት በአንኮበር ከተማም ለአካባቢው ነዋሪዎች በቅርብ ለዕይታ ይበቃል፡፡

በኦውጋዱጉ ቡርኪናፋሶ፣ በህዳር 12-14፣ 2020 በሚደረገው በሶቲጉዪ አካዳሚ/Sotigui Academy የፊልም ሽልማት “የሰላም ባህል፡- በሲኒማ ውስጥ ያሉ ሴቶች ምን አስተዋፅኦ አላቸው?” (The Culture of peace: what contribution from women in cinema?) በሚል አብይ ጉዳይ ዙሪያ የተዘጋጀ ሲሆን፣ እትዮጵያን ጨምሮ የሌሎች የአፍሪካ ሃገራት ተዋናዮች ታጭተዋል፡፡ የሃገራችን እጩ የሆነችው የምስራች ግርማ ከኬንያ፣ ናይጄሪያ፣ ኡጋንዳ፣ ካሜሩን፣ ናሚቢያ፣ ቶጎ፣ ግብፅ፣ ቻድ፣ ጋና፣ ቱኒሲያ ቡሪኪናፋሶ፣ ማላዊ፣ ሴኔጋል፣ ማሊ፣ ሞሪሺየስ፣ አልጄሪያ፣ ኮንጎ፣ ሴንትራል አፍሪካ፣ ታንዛኒያ፣ ሞሮኮ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ጋቦን  ተወዳዳሪዎች  ካባድ ፉክክር ይጠብቃታል፡፡  በሽልማቱ ምሽት በነሃሴ 28፣ 2020 ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው የብላክ ፓንተር ዋና ተዋናይ የነበረው ቻድዊክ ቦስማን ይታወሳል፡፡

ለየምስራች ግርማ መልካም እድል እየተመኘን የፊልም ቤተሰቦችና አድናቂዎቿ በኣካዳሚው የመረጃ መረብ (http://www.academiedessotigui.org/በመግባት “እዚህ ይምረጡ” (vote here) የሚለውን ቦታ በመንካት፣ የኢሜይል አድራሻችሁን በማስገባት፣ ከእጩዎች መሃል ምስሉዋ ያለበትን ምልክት በማድረግ፣ ድጋፋችንን እንድርግላት፣ ሃገራችንንም እናስጠራ፡፡

ለመለጠ መረጃ 
ሲነርጂ ሃበሻ ፊልምና ኮሚኒኬሽን
ስልክ፡ 0911642670/0116680876
ኢሜይል mogest@synergyhabeshafilms.com/
mail@synergyhabeshafilms.comSynergy Habesha Films And Communications In Collaboration With habeshaview And The International Emerging Film Talent Association Presents  Enchained (Quragnaye) A Historical Drama Written & Directed By Moges Tafesse. Following Successful International Festival & Theatrical Engagements Enchained Will Debut As First Film To Stream On New Channel From habeshaviewTV Introducing Emerging Ethiopian And International Filmmakers To A World-Wide Audience.


ENCHAINED IS THE FIRST FILM TO BE PRESENTED ON NEW STREAMING PLATFORM

One of the most successful Ethiopian film releases of 2019 - domestically and internationally - Enchained (Quragnaye), is set as the first feature to screen online on a new movie channel from the already established subscription-based habeshaviewTV, which since 2014 has offered Ethiopian and other international television programs to the world-wide diaspora.Enchained will be presented starting April 18th, 2020. The film runs 90 minutes in Amharic with English subtitles and is unrated. To screen Enchained, available world-wide except for Ethiopia, there is a one-time $5.99 fee for 48 hours, or subscribe to habeshaview monthly or annually to access all its programming, visit: www.habeshaview.com


ENCHAINED (QURAGNAYE), ROTTEN TOMATTOES

In order to free his childhood sweetheart, wanderer student Gobeze is chained and travels with her kidnapper to the royal town to debate and defeat his opponent at a beloved queen's court. Set in 1911, Enchained is a story that delves into an extraordinary traditional law that was abolished during modernity in Ethiopia.

No comments:

Post a Comment

Follow by Email-desc:Subscribe for Free to get all our newest content directly into your inbox.